ቻይና በኢትዮጵያ እምነት እንዳላትና መሉ ድጋፍ እንደምትሰጥ አስታወቀች

ኅዳር 22/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በወቅታዊ እና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ከቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ጦርነት አስመልክቶ ችግሩን ለመፍታት መንግስት እየሄደበት ያለውን መንገድ ለቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስረድተዋል፡፡

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ቻይና ታምናለች ያሉ ሲሆን ይህንንም ያለማንም ጣልቃ ገብነት በራሷ የመፍታት አቅም አላት ብለዋል።

በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም ያለውን እውነት እንደሚመለከቱት ተናግረዋል።