ም/ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቱኒዚያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ጥር 26/2014 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቱኒዚያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦትማን ጄራንዴ ጋር በሁለትዮሽ እና አኅጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እየተካሄደ ካለው 40ኛው የአፍሪካ ኅብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ጎን ለጎን ውይይቱን ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።