ም/ጠ/ሚ/ር ደመቀ ከጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

የካቲት 21/2014 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ እና ዓለም ዐቀፍ ትብብር ሚኒስትር ማሪና ሴሬኒ የተመራውን ልዑክ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመቋጨት መንግሥት የወሰዳቸውን በጎ እርምጃዎች አብራርተዋል፡፡

በዚህም መንግሥት የከፍተኛ የፖለቲካ እስረኞችን ክስ ማቋረጡን እና ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሙን ጠቅሰዋል፡፡

በትግራይ ክልል ተፈፅመዋል የሚባሉ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተም በኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ መብቶች ጽሕፈት ቤት የጋራ ምርመራ ተካሂዶ ውጤቱ ይፋ መደረጉን አስታውሰዋል፡፡

አሸባሪው ሕወሓት በአማራ እና በአፋር ክልል በፈፀማቸው አሰቃቂ ወንጀሎች ዙሪያም ተመሳሳይ ምርመራ እንዲካሄድ መንግሥት እንደሚፈልግ መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW