ም/ጠ/ሚ ደመቀ እና ተሰናባቹ የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር በአገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሁኔታ ላይ ተወያዩ

መጋቢት 9/2014 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና ተሰናባቹ በኢትዮጵያ የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጃሚል አብዱላህ በአገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሁኔታ ላይ ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደሩ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማጠናከር በመስራታቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ሁለቱ ወገኖች በሳዑዲ አረቢያ ስለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሁኔታ የመከሩ ሲሆን ከስደት ተመላሽ ዜጎችን የመመለሻ እና የማገገሚያ መርሃ ግብሮችን በተመለከተ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

አምባሳደር ሳሚ ጀሚል አብዱላህ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ባደረጉት የሶስት ዓመታት የሥራ ቆይታ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ላደረጉላቸው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።

አምባሳደሩ አክለውም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወደፊት ለሚያደርጉት ጥረትና መልካም ምኞት ማመስገናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW