ሦስት የመንግሥት ተቋማት የግንባታ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ተስማሙ

ግንቦት 3/2014 (ዋልታ) ከውጭ የሚገቡ የግንባታ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ሦስት የመንግሥት ተቋማት በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት የከተማና መሠረተልማት ሚኒስቴር፣ ማዕድን ሚኒስቴር እና የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ናቸው።

የከተማና መሠረተልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ፣ የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

የስምምነቱ ዋነኛ ዓላማም ከውጭ የሚገቡ የግንባታ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት በጋራ ለመሥራት መሆኑ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የግንባታ ዘርፍ ለማገዝ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገቡ የግንባታ እቃዎችን በሀገር ውስጥ መተካት ያስፈልጋልም ተብሏል።

ለኮንስትራክሽን ዘርፉ እድገት በቅንጅት ለመስራት የተቋማቱ የጋራ ስምምነት ወሳኝ ሲሆን የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምረት ለመተካትም ጉልህ ጠቀሜታ አለው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW