መስከረም 17/2015 (ዋልታ) ሩሲያና አሜሪካን ጨምሮ የ18 አገራት ኤምባሲዎች ለክርስትና እምነት ተከታዮች የመስቀል በዓል መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ለኢትዮጵያውያን ወንድሞችና እህቶቻችን በዓሉ የደስታ እንዲሆን የተመኘ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲም የመስቀል በዓል የሰላምና የደስታ እንዲሆን ምኞቱን ገልጿል።
የካናዳ፣ ሕንድ፣ እስራኤል፣ ዩናይትድኪንግደም፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ጀርመን፣ ኔዘርላንድስ፣ ዴንማርክ፣ ስዊዘርላንድ፣ ግብጽ፣ ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ኢራን፣ ፓኪስታንና ሜክሲኮ ሌሎች የመልካም በዓል መልካም ምኞታቸውን የገለጹ አገራት ናቸው።
የመስቀል በዓል በመላ ኢትዮጵያ በተለያዩ ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥነ ስርአቶች በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።