ኅዳር 22/2014 (ዋልታ) – ሩሲያ በሞስኮ ከሦስት ዓመት በላይ የቆዩ የአሜሪካ ኤምባሲ ሰራተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማዘዟን አስታወቀች።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ሦስት ዓመት እና ከዚያ በላይ በሩሲያ የኖሩ አሜሪካዊያን ዲፕሎማቶች እስከ ቀጣዩ ጥር 2022 ዓመት ድረስ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡
ሩሲያ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈችው አሜሪካ ባለፈው ሳምንት 27 የሩሲያ ዲፕሎማቶች እና ቤተሰቦቻቸው ከዩናይትድ ስቴትስ እንዲወጡ ውሳኔ ማስተላለፏን ተከትሎ ነው፡፡