ሩሲያ እና ዩክሬን አዲስ የሰላም ድርድር ሊያደርጉ ነው

መጋቢት 19/2014 (ዋልታ) ሩሲያ እና ዩክሬን አዲስ የሰላም ድርድር ሊያደርጉ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

የሩሲያ እና የዩክሬን ዲፕሎማቶች ከመጋቢት 29 አስከ 30 የፊት ለፊት ድርድር እንደሚያካሂዱ የሩሲያ የድርድር ቡድን መሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ ተናግረዋል፡፡

ከዛ በፊትም ዛሬ የሩሲያና ዩክሬን ባለስልጣናት በቪዲዮ ሊንክ ድርድር ማካሄዳቸውን ሲጂቲኤን አስነብቧል፡፡

በዚህም ከመጋቢት 29 እስከ 30 በአካል ለመገናኘት መወሰኑን የሩስያ ፕሬዝዳንት ረዳት የሆኑት ሜዲኒስኪ በቴሌግራም በኩል አሳውቀዋል።

ከየካቲት 28 ጀምሮ ሩሲያ እና ዩክሬን ሦስት ጊዜ ፊት ለፊት የተገናኙ የሰላም ንግግሮች እና ከዚያም ተከታታይ የመስመር ላይ ውይይቶች ያደረጉ ሲሆን ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ቆይተዋል።

አዲሱ የውይይት መድረክ የሚካሄደው የሩሲያ ጦር በዩክሬን የጀመረው የመጀመሪያው ደረጃ ዋና ተግባራት በአጠቃላይ መጠናቀቁን ባለፈው አርብ ካስታወቀ በኋላ ነው።

ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንዳሉት ዩክሬን እንደ የሰላም ስምምነት አካል በድርድሩ ገለልተኛ አቋም ለመያዝ ተዘጋጅታለች።
ነገር ግን ወደ ሪፈረንደም ወይም ሕዝበ ውሳኔ ሄዶ በሦስተኛ ወገኖች ዋስትና ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
የፕሬዝዳንቱ አስተያየት ከሩሲያ ነጻ ጋዜጠኞች ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ የተገኘ መሆኑም ነው የተዘገበው፡፡
ቀጣዩ የዩክሬን እና የሩስያ የፊት ለፊት ድርድር በዚህ ሳምንት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አንድ ወር ያስቆጠረው የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን አፈናቅሎ ለስደትና ጉስቁልና ዳርጓልም ነው የተባለው፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!