ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ከ 8 ሺሕ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

ሐምሌ 9/2014 (ዋልታ) ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበባ እና አከባቢዋ በ20 ካምፓሶች ያስተማራቸውን 8 ሺሕ 236 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርስቲው በሁለተኛ፣ የመጀመሪያ እና ቴክኒክ እና ሞያ የሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ለምረቃ ያበቃው።

ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ 49 ካምፓስ ያለው ሲሆን ከኢትዮጵያ ባለፈ በሱማሊያ ሀርጌሳ ካምፓስ ከፍቶ እያስተማረ መሆኑ ታውቋል።

በቡላ ነዲ