ርዕሠ መስተዳድር እርስቱ እና ዶክተር ሊያ በአርባ ምንጭ መሰረተ ልማቶችን እየጎበኙ ነው

መጋቢት 14/2014 (ዋልታ) የደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር እርስቱ ይርዳ እና የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግንባታቸው እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በርዕሠ መስተዳድሩ የተመራው ልኡክ የአርባምንጭ 2ኛ ደረጃ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት ግንባታ እንዲሁም 8 ነጥብ 7 ኪ.ሜ የሚሸፍነውን የከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ሥራም ጎብኝተዋል።

የከተማውን ኅብረተሰብ የጤና ተደራሽነት ለማሳደግ እየተገነባ ያለውን የአዲስ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል።

የኩልፎን ወንዝ ዳርቻን ተከትሎ እየለማ ያለ አረንጓዴ ፓርክ እና አዳሪ ትምህርት ቤትም መጎብኘታቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።