ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ ከአገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያዩ

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ

ጥቅምት 27/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያዩ።

የሀገር ሽማግሌዎቹ ወራሪውና አሸባሪው ትሕነግ አገር ለማፍረስ የሚያደርገውን የባንዳነት ስራ አውግዘዋል።

አሸባሪው ቡድን ላለፉት ሰላሳ ዓመታት በአገር እና በተለይ በሶማሌ ክልል ያደረሳቸው ግፎችና በደሎች የሚረሱ አይደለም ማለታቸውን የሶማሌ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ዘግቧል።

አያይዘውም አሸባሪውን ለማስወገድና የአገር ኅልውናን ለማስከበር በሚደረገው ትግል የክልሉ ህዝብና የአገር ሽማግሌዎቹ ከመንግሥት ጎን እንደሆኑ ገልፀዋል።