ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋም በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መከሩ

ግንቦት 16/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በተባቡት መንግሥታት ድርጅት ሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ካትሪን ሱዚ (ዶ/ር) ከሚመራ ዓለም ዐቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አመራርና የአምስት አገራት አምባሳደሮች ጋር ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋም በሚቻልበት ዙሪያ መክረዋል፡፡
በዚህም ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ መንግሥት በግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግና በክልሉ የሚኖሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት መልሶ በማቋቋም ረገድ የታቀዱ እቅዶችን ማብራራታቸውን ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።
የተመድ ሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ካትሪን ሱዚ የሚመራውን ዓለም ዐቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎችና አምባሳደሮች መንግሥት በድርቁ ለተጎዱ ዜጎችና በተፈናቃዮች መልሶ ለማቋቋም እየሰራ ላለው ሥራ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡