ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በሆስፒታል ለሚገኙ ታካሚዎችን የምሳ ግብዣ አደረጉ

ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የበጎ ፈቃድ ቀንን ምክንያት በማድረግ በአሶሳ ሆስፒታል የሚገኙ ታካሚዎችን በመጎብኘት የምሳ ግብዣ አካሂደዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ ምክትላቸው ጌታሁን አብዲሳ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ ኢስሀቅ አብዱልቃድር እንድሁም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በሆስፒታሉ በመገኘት ታካሚዎችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን የኢብኮ መረጃ ያመለክታል።