ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ለአዲሱ ክልል ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን 11ኛ ክልል ሆኖ ለተመሰረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ርዕሰ መስተዳደሩ የሕዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ሕገ መንግሥታዊ መብት በለውጡ መንግሥት ተግባራዊ ምላሽ ማግኘቱ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
የፌዴራል ስርዓቱን መሰረት አድርገው የሚቀርቡ የሕዝብ ጥያቄዎችን በወቅቱ ምላሽ መስጠት አገሪቱ በለውጥ ሂደት ስለመሆኗ ማረጋገጫ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ገልጸዋል፡፡
መረጃው የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ነው፡፡