ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እንቅስቃሴን ገበኙ

የካቲት 24/2014 (ዋልታ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የበጋ መስኖ የስንዴ ልማት እንቅስቃሴን ጎበኙ።
በሐዋሳ ዙሪያና ሎካ አባያ ወረዳዎች በአርሶ አደሮችና በባለሃብት በለማ 138 ሄክታር የስንዴ ማሳ ነው እየጎበኙ ያሉት።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መስፍን ቃሬ ከሁለት ወር በፊት የለማው ስንዴ በአሁኑ ወቅት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በበጋ መስኖ የለማው ስንዴ ከሁለት ሳምንት በኋላ ለአጨዳ እንደሚደርስ የተናገሩት ኃላፊው በሄክታር በአማካይ 40 ኩንታል ምርት እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በአርሶ አደሮችና በባለሃብት በበጋ መስኖ በስንዴ የለማውን ማሳ የሲዳማ የክልል ምክር ቤት የግብርና ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባላትና የሁሉም ዘርፍ ቢሮዎች የሥራ ኃላፊዎች እየጎበኙ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!