ሮይተርስ “በኢትዮጵያ የብሔር ማንነትን የሚገልፅ መታወቂያ ግዴታ ሆኗል” ሲል ሃሰተኛ ዘገባን እያሰራጨ ነው


ኅዳር 3/2014 (ዋልታ) ሮይተርስ ኢትዮጵያ ያጸደቀችው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዜጎች የብሔር ማንነታቸውን የሚያመለክት መታወቂያን እንዲይዙ ያስገድዳል ሲል ፍፁም ከእውነት የራቀ ዘገባን አሰራጭቷል።

ኢትዮጵያ በመታወቂያ ካርድ ላይ የብሔር ማንነትን ለማስወገድ በወሰነችበትና እየተገበረች ባለችበት ወቅት ሮይተርስ በዚህ መልኩ መዘገቡ የጣቢያውን ስህተትና ወገንተኝነትን ያሳየ ነው፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዜጎች ማንነታቸውን የሚገልፅ የነዋሪነት መታወቂያ ወይም እንደ መንጃ ፍቃድ ፓስፖርትና ሌሎች ተመጣጣኝ የሆኑ መለያዎችን እንዲይዙ እንጂ ብሔር የሚገልጽ መታወቂያ ያዙ የሚል መግለጫን አልሰጠም፤ እንዲህ ያለ አሰራርም አልተከተለም።

ሮይተርስ አገር ለማፍረስ የሚጣመሩ ስብስቦችን በቀጥታ ስርጭት ሽፋን መስጠትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ የሆነ የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ዘመቻን እያደረገ ነው።