ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሕግ አውጭዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ተጠየቀ

ጥቅምት 5/2015 (ዋልታ) በኢትዮጵያ ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሕግ አውጭዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ጠየቁ።

የሀገር አቀፍ፣ የክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ሕግ አውጭዎች የምክክር መድረክ በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

መድረኩን የከተፈቱት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ባስተላለፉት መልዕክት የጋራ መድረኩ በምክር ቤቶች ተገልፆ በሀገራዊ ጉዳዮች ለመምከርና ልምድ ለመለዋወጥ ያለመ ነው ብለዋል።

ሀገራዊ ምክክር በማድረግ ሰላምን ዕውን ማድረግ የዓመቱ ትኩረት ነው ያሉት አፈ ጉባኤው ለዚህ ደግሞ ምክር ቤቶች ትልቅ ሚና አላቸው ብለዋል።

በዕለቱም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራ ሂደት በኮሚሽነሮቹ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ ሀገራዊ ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ ሰፊ ስራዎች እንደሚጠብቁ ገልፀው የሕግ አውጭዎች ኃላፊነት ጉልህ መሆን እንዳለበት አመልክተዋል።

የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰዓዳ አብዱረህማን በበኩላቸው ሀገርን ወደፊት ለማራመድ በሚደረገው ጥረት ሕግ አውጭዎች ተሞክሮ እንዲለዋወጡ መድረኩ አጋዥ እንደሚሆን መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በምክክር መድረኩ የክልል ምክር ቤቶች የየራሳቸውን ተሞክሮ የሚያቀርቡ ሲሆን በፌዴሬሽን ምክር ቤት በኩል ደግሞ በመንግሥታት ግንኙነት ላይ ምክክር እንደሚደረግ ተገልጿል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW