ሰላም በተለዩ ሰዎች ብቻ ሊመጣ አይችልም፤ ሁላችንም ወደ ሰላምና እድገት ልንመለስ ይገባል – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ

ሚያዝያ 24/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ሰላም በተለዩ ሰዎች ብቻ ሊመጣ አይችልም፤ ሁላችንም ወደ ሰላምና እድገት ልንመለስ ይገባል ሲሉ ገለጹ፡፡

የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተከበረ ባለው 1 ሺሕ 443ኛ ዓመተ ሂጂራ የኢድ አልፈጥር በዓል ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ምላስ እና ቃላት ጥቅም የለውም፤ ጥቅሙ ልባዊና ተግባራዊ ሲሆን ነው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

አንድነት በቃል ሳይሆን በተግባር እንደሆነና ሰላም የሚመጣውም በሕዝብና በመንግሥት አንድነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ምክር ቤቱ ለሰላም መታገሉን የገለጹት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ “አንድነቱን፣ ሰላሙንና ልማቱን እውነት ያድርገው” ሲሉም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡