ሰራዊቱ ከፍተኛ ድል እየተቀዳጀ መሆኑ ተገለፀ


ኅዳር 04/2014 (ዋልታ)
በአርጡማ ፉርሲና ኤፍራታና ግድም ሰንሰለታማ ተራራዎች ወራሪውና ሽብርተኛው ሕወሓት ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑ ተገለፀ፡፡
ጠላትን መመከት ሳይሆን ጠላትን ባለበት ቦታ ቀጥቅጦ የመቅበር ሥራ በቀጣናው በታላቅ ጀብዱ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል።
በግንባሩ አዛዥ የሆኑት ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ረጋሳ በቀጣናው የተሰማራው መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች የጠላትን አገር የማፍረስ ህልም እያከሸፉና ከፍተኛ ድል እየተቀዳጁ መሆኑን ተናግረዋል።
አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ኃይል ያሰማራው ኃይል ባለበት እየተቀበረ ነው ያሉት ብርጋዴር ጀነራሉ የቡድኑ አባላት ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የአካባቢው ማኅበረሰብ ብሎም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እያሳየ ያለው የደጀንነት ተግባር እጅግ አበረታች ነው ብለዋል።
አሸባሪውን ኃይል ለማስወገድ አሁንም የተጠናከረ ርብርብ ያስፈልጋል ያሉት ብርጋዴር ጀነራሉ የጠላትን መውጫና መግቢያ ቦታዎችን እየተከታተለ ለሰራዊቱ ጥቆማ እንዲሰጥም ማሳሰባቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!