ሰብኣዊ አቅርቦትን ጭነው ወደ መቀሌ ይጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች እንዲመለሱ ተገደዱ

ጥር 17/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ትሕነግ በአፋር ክልል በአዲስ መልክ ጥቃት እየፈጸመ በመሆኑ ሰብኣዊ አቅርቦትን ወደ ትግራይ ክልል መቀሌ ይዘው ይጓዙ የነበሩ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ተሽከርካሪዎች እንዲመለሱ ተገደዱ።
ሽብርተኛው ቡድን ተሽከርካሪዎቹን ከግማሽ መንገድ በኋላ እንዲመለሱ ማስገደዱን በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
ቡድኑ በአፋር እንደ አዲስ በጀመረው ወረራና ጭፍጨፋ በአስር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች መፈናቀላቸውንም የጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
የአሸባሪው መሪዎች ሕዝቡን በማስራብ ለፖለቲካ አጀንዳቸው በግልጽ ሲጠቀሙበት እየተስተዋለ መሆኑንም መረጃው ጠቁሟል፡፡
የሽብር ቡድኑ ከዚህ ቀደምም ሰብኣዊ አቅርቦትን ጭነው የሚጓዙ ተሽከርካሪዎችን ሲያግድ ነበር። ወደ ትግራይ የገቡ 1 ሺሕ 10 ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎችም እርዳታን አራግፈው እንዳይመለሱ በማድረግ ለታጣቂዎቹና ከአማራና አፋር ለዘረፋቸው ንብረቶች ማመላለሻነት ሲጠቀም ከርሟል።
በዚህ ሂደት ግን የተሽከርካሪዎቹ ባለቤት የሆነው የዓለም ምግብ ፕሮግራምም ይሁን ሰብኣዊነት ያሳስበናል በሚል ኢትዮጵያ ላይ የወመቱ መንግሥታትና ዓለም ዐቀፍ ተቋማት ድምፃቸውን አጥፍተዋል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!