ሳይሰስቱ ሀገር ማፍቀርንና ሳይታክቱ ሕዝብ ማገልገልን ከወታደሮቻችን እንማር – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ሐምሌ 19/2013(ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሳይሰስቱ ሀገር ማፍቀርንና ሳይታክቱ ሕዝብ ማገልገልን ከወታደሮቻችን መማር እንደሚገባ አሳሰቡ፡፡

ብዙዎቹ የሙያ ዘርፎች ፍላጎትና ተሰጥኦ ቢሹም ለውትድርና ግን ቀዳሚው ጉዳይ ጥልቅ የሆነ የሀገር ፍቅር ስሜት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጸዋል፡፡

እንደ ሌላው ሙያ ውትድርና እውቀትና ጉልበት ብቻ አይፈልግም፤ ደምና አጥንትን ለመገበር ዝግጁ መሆንን ጭምር ይሻል ብለዋል፡፡

ባንዴራችን የሚውለበለበው ከሁሉ በላይ ከጀግና ወታደሮቻችን በሚፈልቀው ትንፋሽ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታከተኝ ሳይሉ ሀገርን ከማገልገል፣ ሳይሰስቱ ፍቅርን ከመስጠት፣ በመርህ ኖሮ ለመርህ ከመሰዋት የበለጠ አኩሪ ገድል እንደማይኖር አስታውቀዋል።

ሻለቃ እና ጋዜጠኛ ወይንሐረግ በቀለ “የወታደር ልጅ ነኝ” ብላ ስትናገር እጅግ በኩራት ነው፤ ወታደር መሆን ደግሞ ኩራቱ  ከፍ ያለ ነው ሲሉ በማህብዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡