ስኬት እያመጣ ነው የተባለው የዲፕሎማሲ ጉዞ

ጳጉሜ 4/2013 (ዋልታ) በሴኔጋል እና ጋና ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለትዮሽና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንም በሳምንቱ ከተባበሩት መንግሥታት የሰላም ጉዳይ ምክትል ጸሐፊና ከሮታሪ ክለብ ፕሬዝዳንት ጋር ውይይት እንዳደረጉ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ መግለጫቸው አብራርተዋል።
በሰላም ጥበቃ ዙሪያ ደመቀ መኮንን ለመንግሥታቱ የሰላም ጉዳዮች ምክትል ጸሐፊ በቂ ማብራሪያና ምላሽ እንደሰጡ ነው አምባሳደር ዲና የተናገሩት።
በአቢዬ የሰላም ማስከበር ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ገዳዩ አንድ የአሜሪካ ሴናተር የኢትዮጵያን የሰላም ማስከበር ሚና ለማንኳሰስ የከፈቱት ዘመቻ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስረድተዋቸዋል ተብሏል።
ኢትዮጵያ በሰላም ጥበቃ ረገድ ትልቅ ሚና ከሚጫወቱ አገራት መካከል ቀዳሚ ናት፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ረድዋን ሁሴንም በሶማሌ ላንድ ጉብኝት ማድረጋቸውና ከፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ጋር ስኬታማ ውይይት ማድረጋቸው ተጠቅሷል።
ውይይቱ በደኅንነት፣ ኢምግሬሽንና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዙሪያ እንደሆነ ቃል አቀባዩ አብራርተዋል።
ከቀጣናው አገራት ጋር በሚኒስቴሩ ዲፕሎማቶች በኩል ስልታዊ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደተሰራ ተገልጿል።
በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በኩል ደግሞ 1 ሺሕ 303 ዜጎች ወደ አገር ውስጥ እንዲመለሱ ተደርጓል።
በደምሰው በነበሩ