ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከ2000 በላይ መጻሕፍትን ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት አበረከቱ

ጥቅምት 22/2017 (አዲስ ዋልታ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከ2000 በላይ መጻሕፍትን እና 25 “ኦርካም ማይ አይ” የተባለ ዐይነ ስውራን አንባቢያንን የሚያግዝ መሳሪያ ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት በስጦታ አበረከቱ፡፡

ለቤተ መጻሕፍቱ የተበረከቱት መጻሕፍት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለአንባቢያን በተለይ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጠቅላላ እውቀትን የሚሰጡ የመጻሕፍት ስብስብ ናቸው።

መጻሕፍቱ “Book for Africa” ከተባለ ድርጅት በድጋፍ የተገኙ መሆናቸው የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።