ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን 1ለ0 አሸነፈ

ሚያዝያ 14/2015 (ዋልታ) የ20ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርኃ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን ገጥሞ 1 ለ 0 አሸነፈ።

በዛሬው ዕለት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ጎል በ71ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ቶጎዋዊው አጥቂ እስማኤል ኦሮ-አጎሮ ነው፡፡

እስማኤል ኦሮ-አጎሮ በሊጉ 19ኛ ግቡን በማስቆጠር የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት መሪነቱን አጠናክሯል።

ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን ወደ 45 ከፍ በማድረግ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ባህርዳር ከነማ በ3 ነጥብ በልጦ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡

ፋሲል ከነማ በ27 ነጥብ በነበረበት 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በ20ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ መርኃ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ በድሬዳዋ ከተማና ሀዋሳ ከተማ መካከል ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።