ቋሚ ኮሚቴው በጀትን ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንግድ መጠቀም እንደሚያስፈልግ አሳሰበ

ሰኔ 23/2013 (ዋልታ) – በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ በ2014 በጀት አመት ረቂቅ በጀት ላይ ይፋዊ የህዝብ ውይይት በአካሄደበት ወቅት አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የሚመደብላቸውን በጀት ከብክነት በጸዳ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ የአስራር ስርዓት መጠቀም እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡

በአለፉት አመታት ከፍተኛ የመንግስት በጀት ብክነት የታየበት በግዥ ስዓቱ ላይ እንደነበር እና አሁንም የቋሚ እቃ ግዥ የአሰራር ስርዓት መስተካከል እንዳለበት በውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየት ተሰጥቷል፡፡
በ2014 በጀት ዓመት የኑሮ ወድነትን እና ስራ አጥነትን ለመቀነስ ምን ታስቧል የሚል ከውይይቱ ተሳታፊዎች ጥያቄ ተነስቷል፡፡
በገንዘብ ሚኒስቴር የበጀት አማካሪ አቶ ተፈሪ ደመቀ ከውይይቱ ተሳታፊዎች ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ለኑሮ ውድነት ትልቁ መንስኤ የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም እንደሆነ ገልጸው ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ መንግስት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በቁርጠኝነት አቅዶ እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ለዚህ ማሳያም የበርሀ ስንዴን በአነስተኛና መካከለኛ የመስኖ ፕሮጀክቶች ለማልማት ዘርፈ-ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ነው አቶ ተፈሪ ያብራሩት፡፡
የስራ እድል ፈጠራን በተመለከተም ለተነሳው ጥያቄ አቶ ተፈሪ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ወጣቶች በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲሳተፉ እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ(ደ/ር) በበኩላቸው መንግስት በሚቀጥሉት አስር አመታት የኢትዮጵያን ብልፅግና ከግብ ለማድረስ አቅዶ እየተሰራ እንደሆነ እና የ2014 በጀት አመት እቅድ የ10 አመቱ መሪ እቅድ የመጀመሪያው ምዕራፍ እንደሆነ አስታውሰው፣ የህዝቡን ኑሮ ከማሻሻል አኳያ ለግብርናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
በሌላ በኩል የአገሪቱ የታክስ አሰባሰብ ክፍተት እንዳለበት የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው እዮብ (ዶ/ር) የታክስ አሰባሰብ ስርዓቱን ለማሻሻል እና የታክስ ማበረታቻ እንዲሮር በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶበት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የሚመደብላቸውን በጀት ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንድ መጠቀም እንዳለባቸው እና በጀቱን ለታለመለት አላማ በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል እንዳለባቸው ነው ሚኒስትር ዴኤታው ያሳሰቡት፡፡
የ2014 በጀት አካል ጉዳተኛ እና የአዕምሮ ውስንነት ያለባቸው ህጻናትን የአካተተ እንዲሆን ይደረጋልም ብለዋል፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ፣በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ያየሽ ተስፋሁነይ ውይይቱን በቋጩበት ወቅት የ2014 በጀት የአገሪቱን የዋጋ ንረት እና ስራ አጥነት እንዲቀርፍ ታሳቢ ተደርጎ የተመደበ በመሆኑ አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የተመደበላቸውን በጀት ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ በመጠቀም ጤታማ ስራዎችን በማከናወን የአገሪቱን ብልግና ለመረጋገጥ የሚያስችል መሆን እንዳለበት ወ/ሮ ያየሽ ማሳሰባቸው ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡