በሀረሪ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

ግንቦት 21/2014 (ዋልታ) የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በክልሉ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

አመራሮቹ “አዲስ ፖለቲካዊ ዕይታ-አዲስ ሀገራዊ እመርታ” በሚል መሪ ሃሳብ እያካሄዱት ከሚገኘው ስልጠና በተጨማሪ በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

አመራሮቹ የዱቄት እና ኦክስጅን ፋብሪካዎችን እንዲሁም በዘንድሮው ዓመት የሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ዝግጅት እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን ነው የጎበኙት፡፡

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር)