በሀረሪ ከሸዋል ኢድ ጋር ተያይዞ የተለያዩ መርኃግብሮች እየተካሄዱ ይገኛሉ

ግንቦት 1/2014 (ዋልታ) በሀረሪ ክልል ከሸዋል ኢድ ጋር ተያይዞ የተለያዩ መርኃ ግብሮች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡

በዛሬው እለትም በክልሉ በ11 ሚሊየን ብር እድሳት የተደረገለት ሼህ አቡበከር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመርቋል፡፡

ትምህርት ቤቱ የጀጎል ግንብን ቅርስ በጠበቀና ለመማር ማስተማር ምቹ በሆነ መልኩ እንደ አዲስ መገንባቱ ተገልጿል፡፡

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይም ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን እንደገለጹት ትምህርት ቤቱ ጥራት ያለው ትምህርት እንዲሰጥና ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚመለከታቸው አካላት ጥረት ይጠይቃል፡፡

በተለይም ተማሪዎች በስነምግባር የታነፁ ሆነው እንዲወጡ መምህራንና ወላጆች ሚናቸውን እንዲያጎለብቱ አሳስበዋል፡፡

የሀረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አሚና አብዱልከሪም በበኩላቸው

ፕሮጀክቱን በ1 አመት ከ6 ወር ለማጠናቀቅ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ለሶስት አመታት መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በጉብኝቱም የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጀላ መርዳሳ፣ የክልሉ ብልፀግና ፓርቲ እና ሌሎች የክልሉና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ ዲያስፖራዎችና የአምስቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልል ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

በተስፋዬ ኃይሉ (ከሐረር ቅርንጫፍ)