በሀረሪ ክልል ለአቅመ ደካሞች ቤት የማደስ መርኃ ግብር ተጀመረ

አቅመ ደካሞች ቤት የማደስ መርኃ ግብር

ግንቦት 2/2014 (ዋልታ) በሀረሪ ክልል ለአቅመ ደካማ ዜጎች ቤት የማደስ መርኃ ግብርን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ አስጀመሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ በክልሉ የተጀመረው ቤት የማደስ ተግባር ዋነኛ መስፈርቱ አቅመ ደካሞችና አረጋዊያንን ለመደገፍ ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል።

የቤቶቹ እድሳት የመጀመሪያ ቅርፃቸውን በያዘ መልኩ ይታደሳልም ብለዋል።

ቤታቸው የሚታደስላቸው አቅመ ደካሞች ቤታቸው ታድሶ እስኪጠናቀቅ ሌላ ማረፊያ ቦታ እንደሚመቻችላቸውም ተጠቁሟል፡፡

ሱራፌል መንግሥቴ (ከሀረር)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW