ሚያዝያ 12/2014 (ዋልታ) በሀረሪ ክልል ባሉ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምገባ ተጀመረ፡፡
በመርኃግብሩ በከተማ እና ገጠር የሚገኙ ከቅደመ መደበኛ እስከ 4ኛ ክፍል ተማሪዎች መካተታቸው ተገልጿል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙኽታር ሳሊህ የምገባው ፕሮግራም ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት የምገባ ፕሮግራም ዋና ዓላማ ተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ አግኝተው ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ ለማስቻል ነው።
በተለይም በትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን መጠነ ማቋረጥ ለመቀነስና ውጤታማ የመማር ማስተማር ተግባራትን ለማከናወን የምግባ ፕሮግራሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አመላክተዋል።
የክልሉ መንግሥት ለተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡን አንስተው በዚህም ከቅድመ መደበኛ እስከ አራተኛ ክፍል ላሉ 35 ሺሕ ተማሪዎች ተጠቃሚ እንደሚደረጉ አብራርተዋል።
በክልሉ የተጀመረው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ዘለቂነት እንዲኖረው ለማስቻል በክልሉ ከሚገኙ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ባለሀብቶች ጋር እየተሰራ እንደሆነ ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!