በሀዋሳ ከተማ የሕዝብ ውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

መጋቢት 14/2014 (ዋልታ) የብልፅግና ፓርቲ በአንደኛ መደበኛ ጉባኤው ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የሲዳማ ክልል ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ውይይቱ የብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በመከረባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ለሕዝቡ ግልጽነትን ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም ከኅብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎች በአመራሩ ምላሽ የሚሰጥባቸው ነው ተብሏል፡፡

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

ደምሰው በነበሩ (ከሀዋሳ)