በሀገር ሰላም እንዲመጣና አዲሱ መንግስት የተረጋጋ እንዲሆን የጸሎት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

መስከረም 25/2014 (ዋልታ) በሀገር ሰላም እንዲመጣና አዲሱ መንግሥት የተረጋጋ እንዲሆን በሃይማኖት አባቶች የፀሎት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ባለው የጸሎት ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የሁሉም ቤተእምነት የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

የፀሎት መርሐ ግብሩ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሲሆን፤ የሚካሄደው ለሀገር ሰላምና በህዝብ የተመረጠው አዲሱ መንግሥት ተረጋግቶ ሀገር እንዲመራ ነው።

በኢትዮጵያና ህዝቦቿ እንዲሁም መሪዎቿ ላይ ባተኮረው ፀሎታቸው የሃይማኖት አባቶቹ በሀገሪቱ መጭው ጊዜ የሰላም የአንድነት፣ የልማትና የብሩህ ተስፋ እንዲሆን መፀለያቸውን ኢዜአ ዘግቧል።