በህገወጥ መንገድ ሲሰሩ የነበሩ 14 የጥበቃ አገልግሎት እና የሀገር ዉስጥ ስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ታገዱ

ሰኔ 25/2013 (ዋልታ) – በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ባካሄደው ኢንፔክሽን ስራ 14 በህገወጥ መንገድ ሲሰሩ የነበሩ የጥበቃ አገልግሎት እና የሀገር ዉስጥ ስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችን ማገዱን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክረተሪያት ጽ/ቤት አስታውቋል።

በዚሁ መሠረት፡-

1.ስብሀቱና ልጆቹ የን/አስ/እና የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግል ማህበር -የካ ክፍለ ከተማ

2.አጋር የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግል ማህበር የካ ክፍለ ከተማ

3.ዋልታ የጥበቃ የስዉ ኃይልና ኮሚሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ

4.አትላስ ጠቅላላ አገ/ኃ/የተ/የግል ማህበር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ

5.ሴፍ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግል ማህበር

ቂርቆስ ክፍለ ከተማ

6.ንስር የጥበቃና የፅዳት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ቦሌ ክፍለ ከተማ

7.ሰላም ሴኩሪቲ ሶሉቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር

የካ ክፍለ ከተማ

8 .ሀይሌ ተክላይና ጓደኞቹ የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሽ/ማህበር የካ ክፍለ ከተማ

9.ክፍሌ ጎሳዮ ሀጎስ እና ወ/ገብርኤል ህ/ሽ/ማህበር

የካ ክፍለ ከተማ

10.ደመላሽ ሀፍቱ እና ጓደኞቻቸዉ የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሽ/ማህበር የካ ክፍለ ከተማ

11.ጎህ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግል ማህበር

ቂርቆስ ክፍለ ከተማ

12.ዮናስ ሮዛ እና መብርሂት የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሽ/ማህበር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ

13.ሃየሎም እና ብርሃኔ የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሽ/ማህበር

ቂርቆስ ክፍለ ከተማ

14.ህሉፍና ሃለፎም የጥበቃ አገ/ህ/ሽ/ማህበር የካ ክፍለ ከተማ