በህፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

ኅዳር 17/2015 (ዋልታ) ህፃናት የነገ ሀገር ተረካቢዎች በመሆናቸው የሚደርስባቸውን አካላዊ፣ ሥነ ልቦና እና ፆታዊ ጥቃቶች በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

“ምቹና ሰላማዊ ኢትዮጵያ ለሁሉም ህፃናት” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ17ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ የህፃናት ቀን ማጠቃለያ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አዘጋጅነት ተከብሯል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሀና የሺንጉስ (ዶ/ር) ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን በህፃናት ላይ የሚደረግ ስርቆት፣ ፆታዊ ጥቃት እና ሥነ ልቦናዊ ተፅዕኖ መከላከል የሁሉም ኃላፊነት የሚጠይቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ በህፃናት ላይ የሚፈፀም ጉዳትን እና ጥርጣሬዎችን ሲመለከት በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ ማድረስ እንደሚገባም አፅንኦት ተሰጥቷል፡፡

በአመለወርቅ መኳንንት

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW