በሊባኖስ ያለህጋዊ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ

መጋቢት 22/2014 (ዋልታ) የተለያዩ ችግር ደርሶባቸው በቤሩት የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ ማኅበር መጠለያ የነበሩ እና ያለህጋዊ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ 36 ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

በቤይሩት የኢፌዴሪ ቆንስላ ጀኔራል ጽሕፈት ቤት ከሊባኖስ የመንግሥት አካላት እና ELMA ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር 4 ህጻናትን ጨምሮ 36 ዜጎችን ወደ አገራቸው እንዲሸኙ ማድረጉን ቆንስላ ጀኔራል ጽሕፈት ቤቱ መግለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!