በሕወሓት ከወደሙ ኢንዱስትሪዎች 27ቱ ማምረት ጀመሩ

ጥር 19/2014 (ዋልታ) በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ከወደሙ ኢንዱስትሪዎች መካከል 27ቱ ማምረት መጀመራቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ፡፡
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮዎች የሥራ ኃላፊዎች አሸባሪው ሕወሓት በደሴና ኮምቦልቻ በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ላይ ያደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል።
ቡድኑ በአጠቃላይ 82 በማምረት ላይ የነበሩና 5 በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ኢንዱስትሪዎች ላይ ውድመትና ዝርፊያ መፈጸሙን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ገልጸው ከእነዚህ መካከል 27ቱ ማምረት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ ቢመለሱም የጥሬ እቃ፣ የመስሪያ ካፒታል እና የመለዋወጫ ችግር እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡
ሥራ የጀመሩ ኢንዱስትሪዎች በመሉ አቅማቸው ወደ ምርት እንዲሸጋገሩና ሥራ ያልጀመሩት ደግሞ እንዲጀምሩ ሚኒስቴሩ ዝርዝር ጥናት አካሂዶ ለሚመለከታቸው አካላት ማስተላለፉንም ተናግረዋል፡፡
ጉብኝቱ በዋናነት በሪፖርት የሚገለጹ መረጃዎችን በአካል በመመልከት መፍትሄ ለመስጠት ያለመ እንደሆነም መናገራቸውን የኤዜአ ዘገባ ያመለክታል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!