በሕወሓት ጥቃት የተፈናቀሉ ኤርትራዊያን ስደተኞች ከበርሃሌ ሠፈራ ጣቢያ ወደ ሰርዶ ተዛወሩ

የካቲት 29/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት በፈፀመው ጥቃት በአፋር ክልል ከሚገኘው በርሃሌ ጣቢያ የተፈናቀሉ ኤርትራዊያን ስደተኞች ወደ “ሰርዶ መዛወራቸው ተገለጸ፡፡
ከስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት  የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ኤርትራዊያኑ ስደተኞች በአፋር በርሃሌ የስደተኞች ጣቢያ እንደቆዩና አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በትናንትናው ዕለት አዲስ ወደ ተቋቋመው ሰርዶ የስደተኞች ማቆያ ጣቢያ ተዛውረዋል፡፡