በመከላከያ ሠራዊቱ የደረሰብን ምት መቋቋም አልቻልንም ሲሉ ምርኮኛ የትህነግ ታጣቂዎች ገለጹ

ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) “በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የደረሰብን ምት ፈፅሞ የምንቋቋመው አልሆነም ሲሉ በሰቆጣ ግምባር እጃቸውን የሠጡ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ገለጹ፡፡

ምርኮኞቹ አያይዘውም ብዙዎች ከአጠገባችን ተደምስሰውብናል፣ አመራሮቻችንም ሞተዋል የተረፉትም ሸሽተዋል በማለት ተናግረዋል፡፡

ጉዕዲ ገ/ኪዳን በሠቆጣ ግምባር እጃቸውን ለመከለከያ ሠራዊታችን ከሰጡ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች መካከል አንዷ ስትሆን አማራን መደምሰስ አለብን የሚል ተልዕኮ እንደተሰጣቸውም ተናግራለች።

በትግራይ ክልል ውስጥ ከፍተኛ አፈና እና የመብት ጥሰት በአሸባሪ ቡድኑ ታጣቂዎች እየተደረገ መሆኑን የገለጸችው ጉዕዲ፤ ምንም እንኳን የጦርነት ፍላጎት ባይኖራትም በቤተሰቦቿ ላይ የሚደርሰውን ወከባ እና እንግልት ላለማየት አሸባሪውን ቡድን መቀላቀሏን ገልፃለች።

ሌላኛው ምርኮኛ ኤልያስ ገብረፃዲቅ የሶስት ወንድ እና የአንድ ሴት ልጅ አባት ሲሆን ከሚሰራበት ቦታ በሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ተገዶ ወደ ማሰልጠኛ እንደተወሰደ መናገሩን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ አመልክቷል።