በመከላከያ ሠራዊት የሰባተኛ ዕዝ ጀብድ ለፈፀሙ አመራሮችና መኮንኖች እውቅና ሰጠ

ጥር 16/2014 (ዋልታ) በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰባተኛ ዕዝ ጀብድ ለፈፀሙ የሠራዊት አመራሮችና መኮንኖች ሽልማትና ዕውቅና ሰጠ።
የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት ጀብድ የፈጸሙ የሠራዊት አባላትን ማበረታታት ለቀጣይ ተልዕኮ ያዘጋጃል።
በዕዙ ምርጥ አዋጊ፣ ተዋጊና አገልግሎ ሰጭ የሠራዊት አባላትና አመራሮች ዕውቅና እና ሽልማት መስጠቱ አገርን የሚያኮራ ተግባር መሆኑንም ገልጸዋል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከአባቶቹ የተረከበውን የአገር ነፃነት ለማስከበር የሚከፍለው መስዋዕትነት በአገር ደረጃ ከፍተኛ ክብር ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ነውም ብለዋል።
በሥነሥርዓቱ ላይ “ትጥቃችንን ሳናላላ ኢትዮጵያን በጀግንነት እንጠብቃለን!”፤ “በተሰጠን ሽልማት ሳንኩራራ የላቀ ስራ ለመፈፀም ሁሌም እንተጋለን”! የሚሉና ሌሎች ተያየዥ መልዕክቶች መተላለፋቸውን የኢዜአ ዘገባ አመልክቷል።