በመዲናዋ ለሚካሄደው የጎዳና ላይ ኢፍጣር የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ

መጋቢት 29/2015 (ዋልታ) በአዲ አበባ ከተማ ለሚካሄደው የጎዳና ላይ ኢፍጣር የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ፡፡

የረመዳን ጾምን አስመልክቶ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ የጎዳና ላይ ኢፍጣር የሚካሄድ ሲሆን የኢፍጣር ፕሮግራሙ በሰላም እንዲከናወን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

“ኢፍጣራችን ለወገናችን” በሚል መሪ ቃል ነገ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከባምቢስ በመስቀል አደባባይ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ ባለው ጉዳና ላይ የኢፍጣር ፕሮግራሙእንደሚካሄድ ተመላክቷል፡፡

ፕሮግራሙ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም ፕሮግሙ በሚካሄድበት ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፡-

* ከቅዱስ ኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
* ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
* ከአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መስቀል አደባባይ
* ከልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፣ በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ
* ከጎማ ቁጠባ ወደ መስቀል አደባባይ

* ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ
* ከካዛንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ
* ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ መስቀል አደባባይ
* ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
* ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
* ከሜትሪዎሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከቀኑ 6:00 ሠዓት እስከ ምሽት 2:00 ሠዓት ድረስ ድረስ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡