በመዲናዋ አዲሱ ትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆነ

አዲሱ ትራንስፖርት ታሪፍ

ታኅሣሥ 8/2014 (ዋልታ) በመዲናዋ የነዳጅ ዋጋን ታሳቢ በማድረግ የትራንስፖርት ዋጋ ላይ ከዛሬ ጀምሮ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 3 ብር ጭማሪ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

በዚህም በሚኒባስ ታክሲ በኪሎ ሜትር 90 ሳንቲም የነበረው ወደ አንድ ብር እንዲሁም በሀይገር እና በቅጥቅጥ በኪሎ ሜትር 40 ሳንቲም የነበረው 45 ሳንቲም በመጨመር መነሻው በሀይገር 3 ብር የነበረው 4 ብር እንዲሁም በሚኒባስ 2 ብር የነበረው 3 ብር ሆኗል።

የታሪፍ ጭማሪው በብዙኃን ትራንስፖርት ላይ እንዳልተደረገ የከተማው የትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ በመግለጫው ገልጿል።