በመዲናዋ የሚገኙ የሀረሪ ማህበረሰቦች የሸዋል ኢድን እያከበሩ ነዉ

ግንቦት 14/2014 (ዋልታ) ታላቁን የረመዳን ወር መጠናቀቅ ተክተሎ ከ6 ቀናት የሸዋል ጾም በኋላ የሚከበረዉን የሸዋል ኢድ ዛሬ በአዲስ አበባ የሚገኙ የሀረሪ ማህበረሰቦች በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበሩት ነዉ።

የሸዋል ኢድ በሀረሪዎች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሲሆን በዛሬዉ እለትም ከኢድ እስከ ኢድ መርሀ-ግብሮች አንዱ እንደሆነ የተነገረለት ይህ ክብረ በአል በመቻሬ ሜዳ መካሄድ ጀምሯል።

በመርሀ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የአሚኔ ዘገባ አመላክቷል።