በሚቀጥሉት 2 ቀናት በኢትዮ-ኬኒያ ድንበር የእንስሳት ክትባት ይካሄዳል

የእንስሳት ክትባት

ጥቅምት 10/2014 (ዋልታ) በክፍለ አህጉራዊ የአርብቶአደር ኑሮ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት አማካኝነት ድንበር ዘለል ተዛማች የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከል በኬንያ እና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢዎች የሚካሄደውን የእንስሳት ክትባት ዘመቻ አስመልክቶ በሞያሌ ከተማ ውይይት ተካሄደ፡፡

በዚህም በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አስተባባሪነት በኢትዮጵያ እና ከኬንያ ድንበር አካባቢዎች የእንስሳት ክትባት ዘመቻው ጥቅምት 11 እና 12/2014 ዓ.ም በይፋ ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡