በማህበረሰብ ጤና መድህን ስራ የህዝብ ተሳትፎን ለማጠናከር ያለመ መድረክ እየተካሄደ ነው

በማህበረሰብ ጤና መድህን ስራ የህዝብ ተሳትፎን ለማጠናከር ያለመ መድረክ የከሙዩኒኬሽን፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች እና የሚዲያ ኃላፊዎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡

ስብሰባውን የከፈቱት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ እንደገለጹት የማህበረሰብ ጤና መድህን ስራ የህዝብ ተሳትፎን ይበልጥ ለማጠናከር ያሰበ ስራ በጋራ ለመስራት ከክልል ኮሙዩኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች እንዲሁም የሚዲያ ኃላፊዎች ጋር በጋራ ለመመካከር የተጠራ ነው ብለዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ ተቋሙ 80 በመቶ አቅዶ ወደ 50 በመቶ አፈጻጸም እንዳለው የኤጄንሲው አማካሪ አቶ አብዱልጀሊል ሁሴን ገልጸዋል።

በመድረኩ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰኽረላ አብዱላሂ የሚዲያውና የኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ የጤና መድህን ስራን በሚያግዝ መልኩ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ስራው  መሰራት እንደሚኖርበት ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ ያለውን የአስተሳሰብ ሁኔታ በመለየት ሁሉን አቀፍ የህብረተሰብ ተሳትፎ እንዲረጋገጥ ተገቢ ትኩረት መደረግ እንዳለበት ተናግረዋል።

እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ ያለውን 50 በመቶ የጤና መድህን አፈጻጸም ወደተሻለ አፈጻጸም ደረጃ እንዲያድግ ተገቢው ስራ እንዲሰራ በማሰብ የተጠራ የጋራ የተሳትፎ መድረክ መሆኑንም አንስተዋል።