በማዕድን ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ካላቸው የውጭ ባለሀብቶች ጋር ውይይት ተካሄደ

መጋቢት 8/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ በማዕድን ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ካላቸው የውጭ ባለሀብቶች ጋር ተወያይተዋል።

ባለሀብቶቹ በኦሮሚያ ክልል በወርቅ፣ ታንታለም እና ኮፐር ፍለጋና ምርት ላይ የመሰማራት እቅድ ያላቸው ሲሆን መንግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንዲገቡ ሁኔታዎችን የምያመቻች መሆኑን ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።