በምርጫ ክልሎች መሰረታዊ የፀጥታ ችግር የለም ያለው ምርጫ ቦርድ

መስከረም 19/2014 (ዋልታ) ነገ መስከረም 20 ምርጫ በሚካሄድባቸው 3 ክልሎች መሰረታዊ የሆነ የፀጥታ ችግር አለመኖሩን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት በተሻለ ጊዜ መድረሱን ገልጾ፣ ባልደረሰባቸው አንዳንድ  ቦታዎች ዛሬ ማምሻውን ተሰራጭቶ እንደሚጠናቀቅ አስታውቋል።

በሐረሪ፣ ሶማሊና ደቡብ የምርጫ ክልሎች የሚከናወነው ድምፅ አሰጣጥ ያለፀጥታ ችግር እንዲከናወን እየተሰራ ነው። በዕለቱ የፌደራልና የክልል ተቋማት፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ምርጫ በሚደረግባቸው ክልሎችና ዞኖች ዝግ ይሆናሉም ተብሏል፡፡

በዙፋን አምባቸው