በምስራቅ ወለጋ ዞን 20 የአሸባሪ ሸኔ አባላት እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የአሸባሪ ሸኔ አባላት
 
ታኅሣሥ 13/2014 (ዋልታ) በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቶ ጊዳ ወረዳ 20 የሸኔ ሽብር ቡድን አባላት እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አስታወቀ፡፡
 
የጉቶ ጊዳ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ሳጂን ከተማ ኦልጂራ እንደገለጹት በቁጥጥር ስር ከዋሉት 20 የአሸባሪው ሸኔ አባላት መካከል 7ቱ መንግስት ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል በሰላም እጃቸውን የሰጡ ናቸው፡፡
 
ከሽብር ቡድኑ አባላት በተጨማሪም 16 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ፣ 11 ኋላ ቀር የጦር መሳሪያ እና ጥይቶች መያዛቸውን ነው የገለጹት፡፡
 
ከዚህ ባለፈም ለሽብር ተግባር ሊውሉ የነበሩ የተለያዩ አልባሳት እና ብሮች መያዛቸውን ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
 
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/waltainfo
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
https://bit.ly/3vmjIZR
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/WALTATVEth
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!