በምግብ ራስን ከመቻል ባሻገር

በምግብ ራስን ከመቻል ባሻገር

በሱራፌል መንግሥቴ

ዩክሬን እና ሩሲያ የዓለማችን ቁንጮ ስንዴ አምራች ሀገራት ናቸው፤ አንድ ሦስተኛ የሚሆነው የዓለማችን የስንዴ ፍላጎት የሚሸፈነው በእነዚህ ሁለቱ ሀገራት ነው፡፡

አሁን ግን በአገራቱ መካከል እየተደረገ ባለው ጦርነት የዓለማችን የስንዴ አቅርቦት እሴት ሰንሰለት በመስተጓጐሉ በዓለም ላይ የስንዴ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እያሻቀበ ይገኛል፡፡

በስንዴ ላይ የታየው የዋጋ ንረት በዚህ የሚገታ እንዳልሆነም የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይገልፃሉ።

በዩክሬን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ተከትሎ ስንዴ አምራች የሆኑ የዩክሬን ለም መሬቶች ሳይታረሱ ፆማቸውን በማደራቸው በሚቀጥለው የምርት ዘመን የሚሰበሰብ ምርት አይኖርም። ይህ ደግሞ የዓለማችን የምግብ ዋስትና የባሰ ስጋት ውስጥ እንዲወድቅ እንደሚያደርግ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ነው፡፡

ሁኔታው ስንዴ ከነዳጅ ጋር የሚገዳደር ቀጣይ የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ የኢኮኖሚ ሀብት እንደሚሆን አሁን በሸማች የዓለም አገራት እየታየ ያለው ሁኔታ ያመለክታል።

በሌላ በኩል ሀገራችን ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት የራሷን ፍላጎት ከማሟላት አልፋ ስንዴን ለዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ ተጨባጭ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ትገኛለች፡፡

ጉዳዩን አስመልክተው ኔሽን ላይ ሀተታ ጽሑፍ ያቀረቡት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ኢትዮጵያ የስንዴ ፍላጎቷን አሟልታ ስንዴን ለውጭ ገበያ የማቅረብ ውጥኗ የጫወታውን ህግ የሚቀይር ነው ይላሉ፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የበጋ ስንዴ ልማት የመጀመሪያው ምዕራፍ ብቻ ከ405 ሺሕ በላይ ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኖ 16 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት ማግኘት ተችሏል፡፡

በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ከ208 ሺሕ ሄክታር መሬት 8 ነጥብ 35 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት መሰብሰቡ ከግምት ውስጥ ሲገባ፤ ኢትዮጵያ ስንዴን ኤክስፖርት የማድረግ ውጥን ስኬታማ እንደሚሆን ማረጋገጫ ነው ሲሉ ኔሽን ጋዜጣ ላይ የሀተታ ጽሑፍ ያቀረቡት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም በጽሑፋቸው አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ የ2014/15 የመኸር እርሻ በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ሀገሪቱ ስንዴን ወደ ውጭ ገበያ የመላክ ውጥንን የማሳካት ተልዕኮን ያነገበ ነው፡፡

በ2014/15 ዓ.ም የመኸር እርሻ የአፈር ማዳበሪያ፣ የምርጥ ዘር፣ የኬሚካልና የግብርና ኖራ ግብዓቶች በስፋት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ መሆናቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ለ2014/15 የምርት ዘመን ለመኸር እርሻ የዋሉ የሰብል ምርጥ ዘርን ጨምሮ እንደ አግሮ ኬሚካሎች ያሉ የግብርና ግብዓቶችን ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ውጤት እንደመጣም ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት።

ባለፈው ምርት ዘመን ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ ብሎም ኅብረተሰቡ የምግብ ዋስትናው እንዲያረጋግጥ ከማድረግ አንፃር የታዩ ውጤቶች ይበል የሚያሰኙ ናቸው።

በዘንድሮ የመኸር እርሻ 13 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ 400 ሚሊዮን ኩንታል እህል ለመሰብሰብ ታቅዶ አስፈላጊው ግብዓት ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በምርት ዘመኑ በአርሶ አደሩ ፍላጎት መሰረት ለማቅረብ ከታቀደው 18 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል አራት ዓይነት የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ ከዩሪያ ውጪ ያለው 15 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል ወይም 85 ከመቶው ማዳበሪያ ውስጥ 14 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተጓጉዞ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል።

ለመኸር እርሻ 155 ሺሕ 348 ኩንታል የተለያዩ ምርጥ ዘሮችን ለአርሶ አደሮች መሰራጨታቸውን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን መረጃ አመላክቷል።

በመኸር እርሻው ለስንዴ ልማቱ ልዩ ትኩረት የተሰጠ ሲሆን በኩታ ገጠም የእርሻ ልማት በመታገዝ የስንዴን ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ እየተሰራ ነው፡፡

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በየጊዜው ምርታማነትን ማሳደግ የሚገባ ሲሆን ለዚህም የመኸር ወቅት ምርትን ከማሳደግ አንፃር ጉልህ ሚና ይጫወታል።

እነዚህን ሁሉ እውነታዎች ወስደን በኢትዮጵያ በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ዘርፍ እየተሰራ ያለውን ሥራ
ዜጎቻችን ከዓለም የስንዴ ዋጋ ግሽበት ብቻ ሳይሆን የምንከላከለው ከስንዴ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ሀገራዊ ጫና ጭምር ነው።

ነገሮች እንደታቀዱ ከሄዱ ደግሞ ለጎረቤት አገራትም እንተርፋለን።
ለዚህ ዕቅድ መሳካት ደግሞ እያንዳንዱ ዜጋ የሚችለውን ሁሉ ማድረግ አለበት።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW