በርካታ የጁንታው ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መማረካቻውን እና መደምሰሳቸው ተገለጸ

ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው

በርካታ የጁንታው ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መማረካቻውን እና መደምሰሳቸውን የመከላከያ ኃይል ሥምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው አረጋገጡ።

በውጭ የሚገኙ የጁንታው ሚዲያዎች የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ቢያናፍሱም የመከላከያ ኃይልና የፌዴራል ፖሊስ በቅንጅት በወሰዱት እርምጃ በርካቶች ተመማረካቸውን ገልጸዋል።  እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑትም ተደምስሰዋል ብለዋል።

የተቀሩት በየእምነት ተቋማትና ገዳማት፣ ዋሻና ሸለቆዎች እራሳቸውን ደብቀው እንደሚገኙ መረጃ እንዳላቸው የገለፁት ጄኔራል ተስፋዬ፣ ጁንታው የሞቱበትን ከፍተኛ አመራሮቹን ከሰብአዊ ርህረሄ ውጭ በሆነ መልኩ እንዳይታወቁ አንገታቸውን ቆርጦ ለየብቻ ስለሚቀብራቸው ለመለየት አዳጋች መሆኑን ተናግረዋል።

የጁንታ ኃይል መደምሰሱንና በየሸለቆው የደበቃቸው የህዝብና የመንግስት ንብረት መያዡን የገለጹት ኃላፊው፣ ጁንታው በህይወት እንዳለ በአንዳንድ አካላት ከውጭ የሚነዛው ፕሮፖጋንዳ ፍፁም ሐሳት መሆኑን አስረድተዋል። መረጃውን ያገኘነው ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ነው፡፡