ሚያዝያ 18/2014 (ዋልታ) በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ የተመራ ልዑክ ሸበሌ ዞን ጎዴ ከተማ ገባ።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ጃኮብሰን እና የኤምባሲው አመራሮች፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሁሴን ቃሲም (ዶ/ር)፣ እና የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር ቢሮ ኃላፊ አሕመድ ያሲን ኢብራሂም በልዑካን ቡድኑ ከተካተቱት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ልዑኩ በጎዴ በሚኖረው ቆይታ በአካባቢው በተከሰተው ድርቅ እና ድርቁን ለመከላከል በቀጣይ በሚደረጉ ዘላቂ ስራዎች ላይ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡