በርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ የተመራው ቡድን በኦሮሚያ ክልል ጢዮ ቀበሌ የለማውን የስንዴ መስኖ ጎበኘ

ጥር 22/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ቡድን በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ጢዮ ቀበሌ የሚገኘውን የመስኖ ልማት ጎብኝተዋል።
ቡድኑ በ641 ሄክታር መሬት ላይ የለማውን የስንዴ ማሳ ነው የጎበኘው፡፡
የስንዴ ማሳውን 826 አርሶ አደሮች ተደራጅተው በክላስተር እያለሙ እንደሚገኝ የክልል ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡